ተማሪ ውድነህ አሰፋ ይባላል፣ ዕድሜው 22 ነው ተወልዶ ያደገው በማይመሽባትና በእንግዳ ተቀባይነቷና በጣፋጭ ፍራፍሬዎቿ እንዲሁም በስኳር አምራችነቷ በምትታወቀው የበረሃዋ እንቁ በመተሐራ ነው።
2014ዓ.ም ላይ በክረምት ወቅት ጊዜ ትምህርት ቤት በመዘጋቱ የክረምት ዕረፍት ጊዜውን ወንድሙ ጋር ለማሳለፍ ድሬደዋ ከተማ በሄደበት ወቅት ትንሽ እራሴን አመመኝ እያለ ተዝለፍልፎ ይወድቃል።
ተማሪ ውድነህ ገና የ22 ዓመት ወጣት ሲሆን በአቅራቢያቸው የሚገኘው ወደ ድል ጮራ ሆስፒታል ለሶስት ወር ክትትል ቢያደርግም ሊሻለው ባለመቻሉ ጥቁር አንበሳ ሪፈር ተፅፎለት በህክምው ለውጥ ማምጣት አልቻለም ነበር በልብ ህመም ምክንያት እስካሁን ከ3 አመት በላይ አልጋ ላይ ውሎ እያደረ ነው።
ቤተሰቦቻቸው አቅመ ደካማ ናቸው አባቱ በህይወት የሉም እናቱ የጉልበት ሥራ እየሰረና በህይወት በሌሉት ባላቸው ጡረታ ነው የሚተዳደሩት እናም ቤተሰቡ ከአቅም በላይ ወጪ አውጥተው ለሶስት ዓመት ያህል ትልቅ ዋጋ እየከፈሉ ከዚህ ደርሰዋል በመጨረሻም ከታዝማ የልብ ህክምና ማዕከል ለልብ ቀዶ ጥገናው ብቻ 885ሺህ ብር ለአጠቃላይ ለህክምናው ወጪ 1.5 ሚሊዮን ብር ተጠይቀዋል። ነገር ግን የተጠየቀው ብር ከቤተሰቦቹ አቅም በላይ በመሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕርዳታ እጃቸውን እንዲዘረጉላቸው ቤተሰቦቹ ይማፀናሉ።
መላው ኢትዮጵያውያን እንዲሁም እናንተ ፍቅር የሆናችሁ ውድ የመተሐራ ልጆች ታናሽ ወንድም ያላችሁ እባካችሁ ወንድማችንን እናትርፈው ፈጣሪ ብድራቱን ይክፈላችሁ በየቀኑ ህመሙ እየተባባሰ የከፋ ደረጃ ላይ ነው እባካችሁ ወንድማችንን ተረባርበን እናድነው🙌
Comments (0)